Fana: At a Speed of Life!

በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ሃገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

“የምሁራን ትብብርና ተሳትፎ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ፎረም ላይ የሃገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንም እየተሣተፉ ነው።

በተጨማሪም በፎረሙ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሠር አፈወርቅ ካሱ ፣የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሣትፎ ማስተባበሪያ ምክርቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሃገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረሙ የሁለት ቀናት ቆይታ እንዳለውም መገለጹን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.