Fana: At a Speed of Life!

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከሚሰሩ ኮንትራክተሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በመሳተፍ ላይ ከሚገኙ ኮንትራክተሮች ጋር የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢጅነር ስለሺ በቀለ ውይይት አካሄዱ።
 
በውይይቱም ኮንትራክተሮቹ የግድቡን የሥራ ክንዉን ሁኔታ በተለይም የተቀናጀ የሥራ ዕቅድ ላይ ለሚኒስትሩ ሪፖርት አቅርበዋል።
 
ከውይይቱ በኋላም ሚኒስትሩ ለኮንትራክተሮቹ ቀጣይ ክንዉኑን በተመለከተ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
 
በቅርቡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ኮሚቴ የግድቡን የሙሌት እና የሥራ ክንውን ሁኔታ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሪፖርት ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።
 
ኮሚቴው በተጨማሪም በግድቡ ዙሪያ ሲደረጉ በነበሩ የሶስትዮሽ የድርድር ሂደቶች ዙሪያ ማብራሪያ አቅርቧል።
 
ኮሚቴው በሪፖርቱ የአባይ ወንዝን ሀይድሮሎጂ፣ የግድቡን የሙሌት ጊዜያት፣ ለ”አስከፊ ድርቅ” እና ድርቅን ለመከላከል የሚሆን ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም መረጃ በሚገባ ለመያዝና ለመለዋወጥ የተዘጋጁ የቅንጅት ስርዓቶች የመሳሰሉ ዐበይት ጉዳዮችን ማካተቱ የሚታወስ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.