Fana: At a Speed of Life!

በቴፒ ነፍጥ ያነሱ አካላትን ወደ ሰላም ለመመለስ የሚያስችል የእርቅና የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‹‹የቴፒና የአካባቢዋ ሰላም በልጆቿ ይረጋገጣል›› በሚል መሪ ሀሳብ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሰላም እጦት ከአካባቢው የተፈናቀሉና ነፍጥ ያነሱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመለሱ የሚያስችል የእርቅ እና የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎቹ “መሪያችን በግንባር ሳሉ እኛ በጥቃቅን ጉዳዮች እርስ በራሳችን ሆድና ጀርባ ሆነን ልንቀጥል አይገባም” በማለት ለእርቅና ሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡
ሃገር ልጆቿን በምትፈልግበት በዚህ ወቅት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንባር በሚገኙበት ወሳኝ ጊዜ መነጣጠል ሳይሆን እርቅ አውርዶ በጋራ ጠላትን መመከት ይገባል ብለዋል፡፡
የቴፒ ከተማ ከንቲባ ገለቲያስ ሻሚ፥ ወቅቱ በህወሓት ጫና እና የማለያየት የፖለቲካ ስርዓት የተበተነው ሁሉ ተሰባስቦ ለጋራ ልማትና ብልጽግና የሚነሳበት ነው ብለዋል።
በአደም አሊ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.