Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ አዲስ ከተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ አዲስ የተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና የቦርድ አባላቱ ኃላፊነታቸውን አውቀው በባለቤትነትና በእውቀት እንዲመሩ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያማታል፡፡
በቀጣይም በዩኒቨርስቲ የትምህርት ጥራት ፣ የሀብት ብክነት መከላከል እና የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ነፃነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ የተናገሩት፡፡
በአዲሱ ሪፎርም÷ የሥርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የዩኒቨርሲቲ የመስክ ልየታ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት መካተታቸው ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.