Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ህብረተሰቡ እስከ መጋቢት 10 ባሉት ቀናት ውስጥ ብቻ አሮጌዉን ብር ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ህብረተሰቡ አሮጌዉን ብር ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ባሉት ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲሱ እንዲቀየር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አሳሰበ።

ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ ሀገሪቱ አሮጌዉን ብር በአዲስ የመቀየሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ባንኩ አስታውሷል፡፡

በክልሉ በነበረዉ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ሳቢያ ብር የመቀየሩ ሂደት ተስተጓጉሎ እንደነበር ያስታወሰ ሲሆን ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ከ100 ሺህ ብር በታች አሮጌ ብር ያላቸዉ እንዲቀይሩ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ተፈቅዶ እንደነበረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

እስካሁን ባለዉ በክልሉ ይቀየራል ተብሎ የሚታሰበዉ አሮጌ የገንዘብ መጠን በአብዛኛዉ የተቀየረ በመሆኑና የሚቀየረዉ አሮጌ ገንዘብ መጠንም በጣም ጥቂት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በክልሉ የተጀመረዉን ብር የመቀየር ሥራ ለማጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን  እንዲቀየር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉ ተጨማሪ ቀናት አሮጌዉ ብር ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር ጥሪ ቀርቧል።

ይህ ማሳሰቢያ የመጨረሻ መሆኑ ታዉቆ የባንክ ቅርንጫፍ በተከፈተባቸዉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በመሄድ ይኸዉ ተግባራዊ እንዲደረግ፤ ባንኮችም በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.