Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል በስምንት አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል – ሌ/ጄ ባጫ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በስምንት አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው ቡድን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ገለፁ፡፡
ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ያለፈው ሳምንት የሰራዊቱ እንቅስቃሴን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤በትግራይ ክልል ትንንሽ ማሰልጠኛዎች እና የጁንታው መሪዎች ጠባቂዎችን ማጥቃትና በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡
ጁንታው ከአሁን በኋላ ሌላ ሰራዊትና ጠባቂ ይዞ ሊቀጥል አይችልም ያሉት ጀነራሉ ይህንን ለማድረግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ተጠቅመናል ብለዋል፡፡
ይህም ጁንታው የሚደርስበትን ጥቃት ለመቋቋም የሚያስችለው አቅም ላይ ባይሆንም ምንም አይነት የሰው ኃይል ኪሳራ እንዳይኖር ታቅዶ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ጁንታው በእነዚህ ስምንት አካባቢዎች ለመቆየት የመረጠው መቐለና ወደ መቐለ የሚወስዱ መንዶችን በመዝጋት የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ደራሽ ዕርዳታ እና አገልግሎት ለማጨናገፍ ነው ብለዋል ጀነራል ባጫ ደበሌ፡፡
ብቻውን የቀረው ጁንታው አሁን በሱዳን በኩል ለማምለጥ እየሞከረ ነው በሚል ለሚናፈሰው ስጋት መከላከያ ሰራዊታችን በሁሉም አቅጣጫ በቂ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ “ጁንታው ሱዳን እንደ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን እንደ መቐለም እንዲርቀው እናደርገዋለን” ነው ያሉት፡፡
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.