Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ እስከ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል።

ዝውውሩ በክልሉ በነበረው ሰላም የማስከበር ዘመቻ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ከታኅሣሥ 26 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአምስት የሥራ ቀናት የተፈቀደ ነበር።

የማራዘሚያ ቀናት የተሰጠው ታህሣሥ 29 ቀን የገና በዓል በመሆኑ ምክንያት እነደሆነም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.