Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል እስካሁን 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ቀርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች እስካሁን 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ መቅረቡ ተገለጸ፡፡

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ ከሚሹ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ውስጥ በመጀመሪያው ምዕራፍ ለሁሉም ድጋፉ መዳረሱን እና በሁለተኛው ዙር ለ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች መዳረሱን ገልጸዋል ።

እስካሁን ድረስ ከሰብዓዊ ድጋፍ ውስጥ መንግስት 70 በመቶ በመንግሥት ሲሸፈን የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ አጋር አካላት ሚናቸው እንዲያድግ መደረጉን አስታውቀዋል ።

በክልሉ ከሚገኙ 92 ወረዳዎች ውስጥ 86 በመቶ ሰብዓዊ ድጋፍ በአጋር አካላት እንደሚቀርብም ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በክልሉ የሚገኙ 1 ሚሊየን ተፈናቃዮችን በፈቃዳቸው ለማቋቋም ሙሉ ሰላም በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች ተፈናቃዮችን የመመለስ፣ ሙሉ ሰላም ባልተመለሰባቸው ቦታዎች ዜጎች ቤተዘመዶቻቸው ባሉበት ስፍራ ድጋፍ እየቀረበላቸው ተጠግተው እንዲኖሩ እንዲሁም ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችን በመገንባት ከክረምት በፊት ተፈናቃዮች እንዲቋቋሙ ለማድረግ አማራጮች እየተተገበሩ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የእርሻ ስራቸው እንዳይተጓጎል የግብርና ግብዓቶች እየቀረበ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ተፈናቃዮች ሲኖሩ፥ ከክረምቱ በፊት ወደ 40 በመቶ ለማውረድ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.