Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤትና አንቀሳቃሾች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤትና አንቀሳቃሾች ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

ምክክሩ በትግራይ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪው ዳግም ወደ ስራ በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ በመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ወሳኝ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአምራች ኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ ወደ ስራ መመለሱ አስፈላጊ በመሆኑ ውይይቱ ማስፈለጉንም ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓትም የህግ ማስከበር ስራው ተጠናቆ የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሀይል አቅርቦትና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጋር የተያያዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በኢንዱስትሪው አንቀሳቃሾች በኩል እንደችግር የሚነሱ ከውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እድሳት ሃይል አቅርቦት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን ለመፍታት ግብረሃይል መቋቋሙም ተነስቷል።

በክልሉ ሰፊ ቁጥር የያዘውን የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳ፣ ብረታብረት እና ሌሎችም ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳረፈባቸው ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ባለቤትና አንቀሳቃሾቹም ቢሟሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተው፥ በግብረሃይሉ የተለዩ ዋና ዋና ችግሮችም ተለይተው ታይተዋል።

የኢንዱስትሪ ሰላምን ማስጠበቅና በመንግስት በኩል የክትትልና ድጋፍ ስራ እንደሚጠበቅም ነው የተነሳው።

በኢንዱስትሪዎቹ በኩልም በሙሉ አቅም ወደ ስራ መግባት የሚያስችል እቅድ ማውጣት እንደሚጠበቅባቸው ነው የተገለጸው።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.