Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የተቋርጠውን የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አስታወቁ።

አሁን በሰሜን ሪጅን ያጋጠመው አደጋ በመቐለ እና በሽሬ ያሉ ዋና ጣቢያዎች ያላቸውን አማራጭ የመገናኛ መስመሮች በሙሉ በመቋረጥ እንዲሁም የኮሜርሻል የኃይል አቅርቦት በማቋረጥ የተከሰተ ነው ብለዋል።

በዚህም የቴሌኮም ጣቢያው ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ አካላት በደህንነት ካሜራ እይታ ውስጥ ለማየት ተችሏል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጉዳዩ በፖሊስ የምርመራ ሂደት ላይ በመሆኑ ውጤቱ ሲታወቅ እንደሚገለፅ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአከባቢው የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር  ሰፊ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፥  በዚህም የተጎዱ መስመሮችን በመጠገን፣ መልሶ በማቋቋም እና አማራጭ ሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪና፣ ማይካድራ፣ በኮረም በከፊል የቴሌኮም አገልግሎት መስጀመር ተችሏል ነው ያሉት።

በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግትን ለማስጀመር አስቸጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የሃይል አቅርቦት መቋረጥ፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች መቆራረት፣ በአከባቢው የሰው ኃይል ለማሰማራት አዳጋች መሆን እና ሌሎች አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሰረታዊ አቅርቦቶች አለመኖር መሆኑ ተገልጿል።

በትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.