Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ዕውነታ እያዛቡ የሚያቀርቡት የኢትዮጵያን ገፅታ ለማጠልሸት የሚፈልጉ አካላት ከንቱ ምኞት ነው- በጄኔቫ ተመድ የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ዕውነታ እያዛቡ የሚያቀርቡት የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማጠልሸት የሚፈልጉ አካላት ከንቱ ምኞት መሆኑን በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አስታወቀ፡፡

በዚህ ጉዳይ ሚዲያውና አለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ መጠለፉ አሳሳቢ መሆኑን መልዕክተኛው ገልጿል፡፡

ዋሺንግተን ፖስት ከሳምንት በፊት ባወጣው እትሙ እንዳስነበበው ከፈረንጆቹ ህዳር እስከ ጥር ወር ብቻ ከ3 ሺህ በላይ የሀሰት መረጃ የሚለቀቅባቸው አዳዲስ የትዊተር አካውንቶች ተከፍተዋል፡፡

እነዚህ አካውንቶች ጥቂት ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀምን በአግባ በማያውቁ ሰዎች እንደተከፈቱም ይታወቃል ነው ያለው፡፡
በተጨማሪም ዋና ስራቸው ለአጭር ጊዜ ለስም ማጠልሻ ብቻ መከፈታቸውን አስነብቧል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራው የስም ማጠልሸት ስራ ውጪ ግን የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እየገባ መሆኑን ቋሚ መልዕክተኛው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው መሰረተ ልማቶች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን፣ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በቅንጅት ድጋፍ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንዳለ እና መንግስትም ክልሉ ላይ የመልሶ ግንባታ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውሷል፡፡

ወንጀል የፈፀሙ አካላትን ወደ ህግ የማቅረብ ስራው ተጠናሮ መቀጠሉንም ነው በመግለጫው ያነሳው፡፡

የህወሓት ጁንታ ቡድን ጥቃት ፈፅሞ መንግስትን አስገድዶ ወደ ህግ ማስከበር ስራ እንዳስገባ፣ የህግ ማስከበር ስራውም መጠናቀቁን እና ሰላም ፈላጊው የክልሉ ህዝብ ቡድኑን ማግለሉን ገልጿል፡፡

የቡድኑ ተላላኪዎች የሀገሪቷን ስም ለማጠልሸት ቢሰሩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ለመረዳት የትግራይን ክልል መጎብኘታቸውን አውስቷል፡፡

የተመድ የደህንነት ረዳት ዋና ፀሐፊ፣ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር በክልሉ በመገኘት ስላለው ተጨባጭ እውነታ መረዳታቸውን አንስቷል፡፡

በአካባቢው በተደረገ ጉብኝትም መንግስት የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እያደረሰ እንዳለ እና አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማትም ገብተው እየሰሩ መሆናቸውን ታዝበዋል ብሏል፡፡

የአለም የምግብ ፕሮግራምም ከመንግስት ጋር በመተባበር ድጋፉን እያቀረበ መሆኑንም አስታውሷል፡፡

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር እስካሁን በተደረገ የሰብአዊ ድጋፍ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ጋር ተደራሽ መሆኑን በመግለጫው አስታውሷል፡፡
ለሰብአዊ ድጋፉም 92 የማሰራጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን ነው ያስታወሰው፡፡

ይሁን እንጂ ያለውን እውነታ በመካድ የሚነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሀገርን መልካም ስም ለማጠልሸት ያለመ መሆኑን ልብ ይሏል ነው ያለው ቋሚ መልዕክተኛው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.