Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 10 ሚሊየን ችግኞች ለተከላ ተዘጋጁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ክልል በዘንድሮ የክረምት ወቅት የሚተከሉ 10 ሚሊየን ችግኞች መዘጋጀታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻ እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና የምግብ ዋስትና ዘርፍ አስተባባሪ ደስታ ገብረ ስላሴ እንደገለጹት፥ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ችግኝ ጣቢያዎች ለተዘጋጁት ችግኞች የመትከያ ጉድጓዶች ቁፋሮ እየተካሄደ ነው።

እስካሁንም በክልሉ 1ሚሊየን 200ሺህ የመትከያ ጉድጓዶች ህብረተሰቡ ባዘጋጃቸው የጋራ እና የግል ቦታዎች ቁፋሮ መደረጉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የመትከያ ጉድጓዶች የማዘጋጀቱ ሰራ አሁንም መቀጠሉን አመልክተው፥ ለዘርፉ ልማት የተቀናጀ እርጥበት የማከማቸት ስራ ትኩረት መሰጠቱንም አስተባባሪው አስረድተዋል።

በተፈጥሮ ሀብት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ለመከላከል በየአካባቢው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸው፥ በዋነኛነት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ለውጥ እያመጡ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.