Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች ድጋፍ ተደርጓል-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ባለው ሂደት ውስጥ በጦርነቱ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወደ 4ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ይህን ያለው በሳምንቱ የተሰሩ ስራዎችን ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡
የሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደገለጹት÷ በዚህ ሳምንት በተለያዩ የውጭ ሀገራት ያሉ አምባሳደሮችና ኤምባሲዎች የሰሯቸው በርካታ የዲፕሎማሲና ዜጋ ተኮር ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
በዚህም በኢኮኖሚው እና በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዞ 60 ወታደሮች ተጠርጥረው ለህግ መቅረባቸውንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለሚያደርገው ፓርትነር ሺፕ ፎር ኢትዮጵያ÷ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሰማራ መደረጉ የሚታወስ ነው ብለዋል፡፡
በውስጡም ሳፋሪኮምን ጨምሮ 5 የሚጠጉ የቴሌኮም ድርጅቶችን መያዙ ይታወቃል ይህ ደግሞ ትልቅ ለውጥ ነው ብለዋል፡፡
ከዚያም ባለፈ በጤና፣ በትምህርትና በግብርናው ዘርፍም ትልቅ አስተዋጽ እንደሚያበረክቱ አንስተዋል፡፡
በስራ ዕድል ፈጠራውም ወደ 1ነጥብ 5 ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡
በዚሁ ስምምነት ላይ ለመሳተፍ የመጡት የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ቆይታ በርካታ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅሰዋል።
ይህም የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት ጠንካራ እንዲሆን ያግዛልም ነው ያሉት፡፡
ስለ አምባሳደሮች ዲፕሎማሲና ዜጋ ተኮር ስራዎች በተለይ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በውጭ ሀገር ላሉ ዜጎች በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡
ከዚሁም ጋር ተያይዞ በካናዳ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያን ወደ 300 ሺህ ዶላር መሰብሰቡን አምባሳደሩ አንስተዋል፡፡
ከዜጎች ጋር ተያይዞም 1136 የሚሆኑ ዜጎች ከሳውዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው በሰላም እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከትግራይ ጋር የተያያዘ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አንስተዋል፡፡
በዚህም ውይይት አምባሳደሮች ፣ከመንግስት ባለስልጣናት ፣ የተባባሪ አገራት አምባሳደሮች፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላ ትና ሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች መሳተፋቸውን አንስተዋል።
አምባሳደሩ አያይዘውም በትግራይ ክልል 70 በመቶ የእርሻ መሬት ለእርሻ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው÷ ይህም 1ነጥብ 2 ሚሊየን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
በዘቢብ ተክላይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
2,807
People Reached
1,195
Engagements
Boost Post
448
54 Comments
17 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.