Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ዘንድሮ ለ258 ሺህ ሰዎች የስራ እድል እየተመቻቸ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተያዘው ዓመት 258ሺህ ያህል ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የስራ እድል ለማመቻቸት እየተሰራ መሆኑን የትግራይ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ እንዳሉት፥ የክልሉ መንግስት ከግብርናው ዘርፍ በተጨማሪ ለማምረቻ ዘርፍ እና  ለማዕድን ልማት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ የስራ እድል እየተመቻቸ ነው።

በዚህም 258 ሺህ ሰዎች አዳዲስ የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው፤ ይህም ዘንድሮ 20 በመቶ ላይ ያለውን የክልሉ የስራ እጥነት መጠን እስከ አምስት በመቶ ለመቀነስ እንደሚያስችል ተመልክቷል።

“ዘንደሮ በክልሉ የተሻለ ምርት ሊገኝ እንደሚችል ይጠበቃል” ያሉት አቶ ዳንኤል፣ ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህሉን ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሳደግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

”ክልሉ የደረሰበት ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ በምሁራን እየተጠና ነው” ያሉት የቢሮው ኃላፊ ጥናቱ የክልሉን ሶስተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማዘጋጀት እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.