Fana: At a Speed of Life!

በቶማስ ሳንካራ ግድያ የቀድሞው የቡሪኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌይስ ኮምፓኦሬ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቡሪኪና ፋሶ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተወዳጅ በነበሩት እና ሀገሪቱን ለተወሰኑ ጊዜያት ከመሩት ቶማስ ሳንካራ ግድያ ጋር ተያይዞ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌይስ ኮምፓኦሬ ላይ በሌሉበት ክስ መሰረተ።

በፈረንጆቹ 1983 ስልጣን ይዞው እስከ 1987 ቡሪኪና ፋሶን የመሩት ቶማስ ሳንካራ በወቅቱ የቅርብ ወዳጃቸው በነበሩት ብሌይስ ኮምፓኦሬ  መፈንቅለ መንግስት ተካሂዶባቸው በ37 ዓመታቸው ከ12 ሌሎች ባለስልጣናት ጋር መገደላቸው የሚታወቅ ነው።

ፍርድ ቤቱም ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱን እስከ ፈረንጆቹ 2014 የመሩትን ብሌይስ ኮምፓኦሬ በግድያ እና በመንግስት የፀጥታ አካላት ጥቃት በመፈፅም ክስ መስርቷል።

ኮምፓኦሬ በ2014 ስልጣናቸውን ለማራዘም ሲንቀሳቀሱ በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ተወግደው በኮት ዲቫር ጥገኝነት ጠይቀው እንደሚገኙ ይነገራል።

ቡሪኪና ፋሶን ለ27 ዓመታት ከመሩት ኮምፓኦሬ በተጨማሪ የቀኝ እጃቸው ጊልቤርት ዴንዴር እና የደህንነት አለቃ የነበሩትን ጨምሮ 13 ባለስልጣናት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የቶማስ ሳንካራ ቤተሰቦችን የወከሉት ጠበቃም ሁኔታውን ድል እና በትክክለኛ አቅጣጫ መጓዝ ነው ሲሉ መግለፃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በርካታ የቡሪኪና ፋሶ ዜጎች ቶማስ ሳንካራን ብሄራዊ ጅግናቸው መሆኑን የሚገልጹ ሲሆን ታዋቂ የፓን አፍሪካዊነት አቀንቃኝ ነበር።

በአንድንድ ወገኖች የአፍሪካ አህጉር ቼ ጉቬራ ተብሎ በሚጠራው ቼ ጉቬራ ግድያ ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ባሻገር ምዕራባውያን ሀገራት ይጠረጠራሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.