Fana: At a Speed of Life!

በቻምፒየንስ ሊጉ ሙኒክ ባርሴሎናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎታል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

በሊዝበን በተደረገው ጨዋታ የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ባርሴሎናን 8 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፎታል፡፡

በጨዋታው ቶማስ ሙለር እና ተቀይሮ የገባው ፊሊፔ ኮቲንሆ ለሙኒክ ሁለት ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

ቀሪዎቹን ጎሎች ደግሞ ፐርሲች፣ ናብሪ፣ ጆሹዋ ኪሚች እና ሮበርት ሎዋንዶውስኪ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

ለባርሴሎና ደግሞ አላባ በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም ሉዊስ ሱዋሬዝ የማስተዛዘኛ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

ድሉን ተከትሎ ባየርን ሙኒክ ለ12 ጊዜ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችሏል፡፡

የካታላኑ ክለብ በበኩሉ ከአምስት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፎ ተሰናብቷል፡፡

ሙኒክ ከማንቼስተር ሲቲ እና ከሊዮን አሸናፊ በግማሽ ፍጻሜው የሚጫወት ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.