Fana: At a Speed of Life!

በቻምፒየንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሄደዋል፡፡

ኢትሃድ ላይ በተደረገ ጨዋታ ባለሜዳው ማንቼስተር ሲቲ ቦሩሲያ ዶርትመንድን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ኬቪን ደ ብሩይነ እና ፊል ፎደን ለባለሜዳዎቹ ሲያስቆጥሩ ማርኮ ሬውስ ዶርትመንድ ተስፋ የሰነቀባትን ጎል አስቆጥሯል፡፡

በሌላ ጨዋታ ወደ ስፔን ያቀናው ሊቨርፑል በሪያል ማድሪድ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

ቪኒሺየስ ጁኒዬር ሁለት እንዲሁም ማርኮ አሴንሲዮ ደግሞ አንደኛዋን ጎል ለሪያል ማድሪድ አስቆጥረዋል፡፡

ለሊቨርፑል ደግሞ ሞሃመድ ሳላህ የማስተዛዘኛዋን ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.