Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ሁቤይ ግዛት በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ሁቤይ ግዛት በኮሮና ቫይረስ አዲስ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተነገረ።

በግዛቲቱ ትናንት ብቻ ወደ 242 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል።

ከዚህ ባለፈም 14 ሺህ 840 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ይህም ቫይረሱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል።

ትናንት የተመዘገበው የሟቾቹ እና አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ እና የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በእጅጉ ጨምሮታል።

አሁን ላይ በቻይና በቫይረሱ ሳቢያ 1 ሺህ 350 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

አዲስ ከወጣው መረጃ ጋር በተያያዘ ሁለት የግዛቲቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነት መነሳታቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.