Fana: At a Speed of Life!

በቻይና አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህጻን በኮሮና ቫይረስ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ውሃን ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የተወለደ ጨቅላ ህጻን በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተሰማ።

ህጻኑ ከተወለደ ከ30 ሰዓታት በኋላ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህም በቫይረሱ የተያዘ በእድሜ ትንሹ ሰው ያደርገዋል ነው የተባለው።

የሕፃኑ እናት ከመውለዷ በፊት በተደረገላት ምርመራ በቫይረሱ መያዟ የተረጋገጠ ሲሆን፥ ቫይረሱ እንዴት ወደ ህጻኑ እንደተላለፈ ግን ግልጽ አይደለም ተብሏል።

3 ነጥብ 25 ኪሎ ግራም ክብደት ይዞ የተወለደው ህጻን አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ክትትል እየተደረገለት መሆኑም ተጠቁሟል።

ቫይሰሩ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በውሃን ሆስፒታል የህጻናት ሀኪም ዜንግ ሊንግኮንግ ተናግረዋል።

ህፃኑ ከተወለደ በኋላ ከእናቱ ጋር የሚኖረው የጠበቀ ግንኙነት በቫይረሱ ለመያዙ ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።

መነሻውን ውሃን ከተማ ባደረገው ቫይረስ እስካሁን 563 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 28 ሺህ 18 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.