Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ከሶስት ወራት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ከሶስት ወራት በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

የሃገሪቱ ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን እንዳስታወቀው በሃገሪቱ 101 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 89 ሰዎች በምዕራባዊቷ ዢንጂያንግ ግዛት ነዋሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከሚያዚያ ወር ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ዓለም ላይ 16 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ659 ሺህ በላይ የሆኑት ለህልፈት ሲዳረጉ ወደ 9 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ አሜሪካ፣ ብራዚል እና ህንድ ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.