Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የታየው ገዳይ ቫይረስ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን መያዙ ተነገረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በገዳይነቱ አደገኛ ነው የተባለለት ቫይረስ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደያዘ ተገለፀ።

እስካሁን 41 ሰዎች በዚህ ቫይረስ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ ሲሆን፥ ባለሙያዎች የተያዙት ሰዎች ቁጥርን 1 ሺህ 700 አድርሰውታል።

በውሃን ከተማ እስካሁን በቫይረሱ ሁለት ሰዎች ሞተዋል ተብሏል።

በጃፓንና በሆንግ ኮንግም አንድ አንድ ሰው በቫይረሱ የተያዘ ሰው እንደተገኘባቸው ነው የተገለፀው።

ከዚህች የቻይና ከተማ ቀጥታ በረራ የሚደረግባቸው ሀገራት ከከተማዋ ተነስተው በሚመጡ አውሮፕላኖች ተሳፋሪዎች ላይ በአውሮፕላን ማረፊያዎቻቸው ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል።

ሲንጋፖርና ሆንግ ኮንግ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ መርመራውን ቀድመው ጀምረዋል።

የቻይና ባለስልጣናት ቫይረሱ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ ባህሪ እስካሁን እንዳልታየበት ተናግረዋል።

በአውሮፓውያኑ 2002 ላይ በዚያው በቻይና የዚህ ቫይረስ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን፥ በወቅቱ 774 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.