Fana: At a Speed of Life!

በቻድ በቦኮ ሃራም በተፈጸመ ጥቃት 14 ሰዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራባዊ ቻድ በታጣቂው ቦኮ ሃራም በተፈጸመ ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ።

በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪ 5 ሰዎች ሲቆስሉ 13 ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት ስፍራ ከናይጀሪያ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና ቦኮ ሃራም በአካባቢው ለሚፈጽመው ጥቃት እንደ መነሻ የሚገለገልበት ስፍራ መሆኑ ይነገራል።

አካባቢው ቻድ ከካሜሩን፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ጋር የምትዋሰንበት አካባቢ ነው።

ቦኮ ሃራም በፈረንጆቹ 2009 ሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ውስጥ የትጥቅ ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ፥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል በርካቶችን ደግሞ ከቀያቸው አፈናቅሏል።

ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው የሚያደርሰውን ጥቃት ለመከላከልም ወታደራዊ ጥምረት ቢቋቋምም የታሰበውን ያክል ውጤታማ እንዳልሆነ ይነገራል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.