Fana: At a Speed of Life!

በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወኃት ውስጥ ባለው ህገወጥና ዘራፊ ቡድን በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው፡፡

የልዩ ኃይል አባላቱ ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ጋር መዋጋታችን ትክክል አልነበረም ብለዋል፡፡
ይህንን በማመንም በሰላማዊ መንገድ ወደ አማራ ክልል ገብተናል ነው ያሉት፡፡

“እኛ የቆምንለት ዓላማ ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንጂ ለህወኃት ህገወጥ ቡድን አይደለም” ያሉት የልዩ ሃይል አባላቱ ወደ አማራ ክልል ከገቡ በኋላም በእንክብካቤ እንደተያዙ ተናግረዋል፡፡

“የትግራይ ህዝብ በህገወጡ የህወኃት ቡድን ከሚደርስበት በደል ለመወጣት ከሃገር መከላከያ ሰራዊት እና ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር እንዲሰለፍም እንጠይቃለን” ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ የክልሉ የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.