Fana: At a Speed of Life!

በነገሌ ከተማና በምዕራብ ወለጋ ላሎ አሰቢ ወረዳ ለችግረኛ ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣መስከረም 27፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የነከሌ ከተማና በምዕራብ ወለጋ ዞን በላሎ አሰቢ ወረዳ ለሚገኙ 371 የችግረኛ ቤተሰብ ህፃናት የትምህርት መርጃ ቁሳቁና የደንብ ልብስ ተበረከተ።
የነገሌ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በዛብህ በከተማው ለሚገኙ 181 ተማሪዎች ባጠቃላይ 2 ሺህ 181 ደብተር፣ 543 እርሳስና እስክሪብቶ፣ 15 የደንብ ልብስ ድጋፍ መደረጉን ገለጹ።
እንደ ሃላፊው ገለጻ ከተጠቀሱት ተማሪዎች በተጨማሪ ለአንድ አካል ጉዳተኛ ተማሪ የመንቀሳቀሻ ወንበር(ዊልቼር) ድጋፍ ተደርጓል።
ስጦታው የተበረከተው በእድሜ መግፋትና በአካል ጉዳት መስራት ለማይችሉና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ህጻናት ወላጆች እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ድጋፉ ከነገሌ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ነጋዴዎች፣ ከመንግስት ሰራተኞችና ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተሰበሰበ እንደሆነም አብራርተዋል።
የጉጂ ዞን ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተወካይ አቶ በሃይሉ ብሩ “እኛ ኢትዮጵያዊያን እርስ በእርስ በመረዳዳትና በመደጋገፍየችግር ቀንን የማለፍ የአኩሪ ባህል ባለቤት ነን” ብለዋል።
በዞኑ በዚህ አመት ብቻ 520 ሺህ መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጀት ተጠናቆ የተማሪዎቹ ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በላሎ አሰቢ ወረዳ ላሉ 190 የችግረኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረጓል።
የላሎ አሳቢ ወረዳ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት ዳንኤል እንዳሉት በመማሪያ ቁሳቁስ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ በተሰራው ስራ ለተማሪዎቹ ድጋፉን ማድረስ ተችሏል።
ድጋፉ ከወረዳው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን ነው ሃላፊዋ የገለጹት።
ከድህነትና ከኑሮ ውድነት የተነሳ በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት መገኘቱን የተናግሩት ሃላፊዋ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ 100 ሺህ ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ እንደሆነም ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.