Fana: At a Speed of Life!

በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ 500 ዜጎችን ወደ አገር ሊመልስ  ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ 500 ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ ሊመልስ መሆኑን አስታወቀ።

በስደተኞች መጠለያ የሚኖሩት እነዚህ  ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፍላጎት ያላቸው እና  በፈቃደኝነት   መሆኑም ነው የተገለጸው።

ኤምባሲው ቦታው በመገኘት የጉዞ ሰነድ የሰጠ ሲሆን በቀጣዮቹ ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ገልጿል።

በዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ያመለከቱ ሲሆን ÷ኤምባሲው በቀጣይ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የጉዞ ሰነዱን እንደሚሰጥ በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.