Fana: At a Speed of Life!

በናይጀሪያ በቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጀሪያ ኦንዶ ክልል በሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርሲቲያን ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
 
የግዛቷ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ታጣቂዎች ድርጊቱን የፈጸሙት፥ ምዕመናን ቅዱስ ፍራንሲስ በተሰኘ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአምልኮ አገልግሎታቸውን እያከናወኑ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
 
በተፈጸመው ጥቃትም እስካሁን ቢያንስ 50 የሚሆኑ ዜጎች ህይወት ያለፈ ሲሆን÷ከሟቾቹ ውስጥም አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
 
የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሃሪ ጉዳዩን አስመክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን አገራችን እኩይ አላማ ላነገቡ አፍራሽ ኃይሎች አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡
 
ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንደሚያገኙ የገለጹት ፕሬዚዳንት ቡሃሪ÷ ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶችም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
 
ለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩንም ቢቢሲ እና ቲ አር ቲ በዘገባቸው አመላክተዋል፡፡
 
በናይጄሪያ ዋና ከተማዋን አቡጃ ጨምሮ በበርካታ ክልሎች ውስጥ መሰል ጥቃቶች በተደጋጋሚ እንደሚፈጸሙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
 
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.