Fana: At a Speed of Life!

በናይጄሪያ ከ1 ሺህ 800 በላይ ታራሚዎች ከእስር ቤት  አመለጡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 (ኤፍ .ቢ.ሲ) በናይጄሪያ ታጣቂዎች በማረሚያ ቤት ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ  1 ሺህ 844 ታራሚዎች ማምለጣቸው ተገለፀ።

ታጣቂዎቹ በኦዌሪ ከተማ ወደ ሚገኘው  ማረሚያ ቤት በማቅናት ተጠቀጣጣይ መሳሪያ በመጠቀም የአስተዳደር ህንፃውን በማፍረስ  መግባታቸው ተነግሯል።

ካመለጡት ታራሚዎች መካከል ስድስቱ ወደ እስር ቤቱ ሲመለሱ 35 የሚሆኑ ታራሚዎች ደግሞ ከእስር ቤቱ ለማምለጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የናይጄሪያ ማረሚያ ቤቶች አገልግሎት 1 ሺህ 844 ታራሚዎች ማምለጣቸው ለቢቢሲ አረጋግጧል።

በፒክ አፕ ተሽከርካሪ እና አውቶቡስ ኦዌሪ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል የደረሱት ታጣቂዎቹ ከባድ የጦር መሳሪያ  የታጠቁ መሆናቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል።

ታጣቂዎቹ ተወንጫፊ ሮኬቶች ፣ ተቀጣጣይ መሳሪያ  እና ዘመናዊ ክላሾችን የያዙ መሆናቸው ተነግሯል።

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ድርጊቱን ሙሀመዱ ቡሃሪ በስርዓት አልበኞች የተፈፀመ የሽብርተኝነት ተግባር ሲሉ ገልጸውታል።

ፕሬዚዳንቱ የፀጥታ ሀይሎች ጥቃቱን የፈፀሙትን  እና ያመለጡ  ታራሚዎችን  በቁጥጥር ስር እንዲያወሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

መንግስት ጥቃቱን የፈፀመው ከናይጄሪያ ለመገንጠል የሚንቀሳቀሰው የቢያፍራ ህዝቦች ንቅናቄ ነው ቢልም ንቅናቄው ግን በመንግስት የቀረበውን ክስ ውደቅ አድርጓል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.