Fana: At a Speed of Life!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲበንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽኅፈት ቤት ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

ባለጉዳዩ ለከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረሱት ጥቆማ ÷ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል የጽህፈት ቤት ሃላፊውን ገንዘቡን ሲቀበል በቁጥጥር ስር መዋሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንጀል ክትትል ሃላፊ ኮማደር አወሉ አህመድ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ጥቆማውን የሰጡትን ግለሰቦች ከማመስገኑም ባለፈ ህብረተሰቡ ህጋዊ ለሆነ አገልግሎት ጉቦ መሰል እጅ መንሻ የሚጠይቁ የመንግስት መዋቅር ላይ ያሉ አካላትን በማጋለጥ እና ጥቆማ በመስጠት ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡን ከከንቲባ ጽኅፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.