Fana: At a Speed of Life!

በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18 ሚሊየንን መሻገሩ ተገለጸ፡፡
በአለም ዙሪያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ የመጣው የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በህክምና የተረጋገጡ ብቻ 18 ሚሊየን 42ሺህ 795 ሰዎችን ይዟል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 65 ሺህ 777 ሰዎች በጽኑ ህመም ውስጥ እንደሚገኙ ነው የተነገረው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ወረርሽኙ የ689 ሺህ 164 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡
በቫይረሱ ተይዘው ያገገሙት ሰዎች ቁጥርም ከ11 ሚሊየን 340 ሺህ 879 ማለፉን የወርልድ ሜትር ሪፖርት ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.