Fana: At a Speed of Life!

በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ32 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ32 ሚሊየን አልፏል።

በቻይናዋ ውሃን ግዛት ከተከሰተ ከስምንት ወራት በላይ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ እስካሁን 32 ሚሊየን 97 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ላይ ተገኝቷል።

በቫይረሱ ተይዘው ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ981 ሺህ በላይ ሆኗል።

በዓለም ዙሪያ እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 23 ሚሊየን 680 ሺህ በላይ መሆኑም የወርልድ ኦ ሜትር መረጃ ያመለክታል።

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ኮሎምቢያ በርካታ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙባቸው ሃገራት መካከል ከአንድ አስከ አምስተኛን ደረጃን ይዘዋል።

ደቡብ አፍሪካም ከፔሩ፣ ሜክሲኮ እና ስፔን ቀጥሎ በዘጠነኛ ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን፥ ኢትዮጲያ ከ215 ሀገራት መካከል 48ኛ ሆናለች።

ምንጭ፡- ወርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.