Fana: At a Speed of Life!

በአሌ ልዩ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ14 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የልዩ ወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ደመቀ ደምሴ ለኢዜአ እንደገለፁት÷ አደጋው የደረሰው መነሻውን አርባ ምንጭ በማድረግ ወደ ጅንካ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በወረዳው ቀርቀርቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ላጋኖ በሚባል አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-03348 ደሕ በሆነ አውቶብስ ውስጥ ይጓዙ ከነበሩት 45 መንገደኞች መካከል በአደጋው የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት አዛዡ÷ በአደጋው ስድስት ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥማቸው ስምንቱ ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

ትናንት ከቀትር በኋላ የደረሰው የትራፊክ አደጋ የቆሰሉ መንገደኞች በገዋዳ ጤና ጣቢያ ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን÷ ከባድ ጉዳት ያጋጠማቸው ወደ አርባምንጭና ሶዶ ሆስፒታሎች መላካቸውን ተናግረዋል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ መንገደኞች አስከሬን ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን ገልጸው÷ የአደጋው ምክንያት ተሽከርካሪው ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር እንደሆነም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.