Fana: At a Speed of Life!

በአሚሶም ሴክተር ሶስት ሰላም ማስከበር ተልኮ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ስድስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ዘማቾች ሜዳይ ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ሴክተር ሶስት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ስድስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ዘማቾች ሜዳይ ተሸለሙ፡፡
የሜዳልያውን የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አለሙ አየነ እና የሰባተኛው ዙር ሰላም አስከባሪ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ አልብሰዋል ።
ብርጋዴር ጄኔራል አለሙ አየነ በስነ ስርዓቱ ላይ ÷ መንግስትና ህዝባችን በከሃዲው ጁንታ እና በሌሎች ግብረ አበሮች ላይ በአጭር ጊዜ ህግን በማስከበር ውጤታማ ዘመቻ ተካሄዶ ህገ መንግስቱም ተከብሯል ብለዋል፡፡
ዘመቻው መንግስትና ህዝብ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያስመሰከሩበት፣ በታሪክ ታላቅ ገድል የተፈፀመበት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
አያይዘውም አባላቱ ተልዕኳቸውን ሃላፊነት በተሞላበት መንፈስ የአፍሪካንና የሃገራቸውን ክብር በማስጠበቅ በድል እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.