Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልልና በውጪ ሀገር የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል እና በውጪ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች 29 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ድጋፎችን በወሎ ግንባር ለተሰለፈው የመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ÷ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ለኢትዮጵያ ቀርቶ ለዓለም ህዝብ ጠቃሚ ያልሆነ አውዳሚ እና ዘራፊ ቡድን ነው ብለዋል።
ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ይህንን ቡድን ለመደምሰስ የሚያደርገው ርብርብ የሚያስደስት እና የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪው ህወሓት ሙሉ በሙሉ እስከሚደመሰስ ድረስ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊታችን የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።
በግንባሩ የሚገኙት የመከላከያ ከፍተኛ አመራር በበኩላቸው÷ ግንባር ድረስ በመገኘት ለተደረገው ድጋፍ በመላው ሠራዊት ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.