Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ23 ሚሊየን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሦስት ወረዳዎች ከ23 ሚሊየን ቶን በላይ የግራናይት ክምችት መገኘቱን የአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የግራናይት ክምችቱ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኙት ባሶ ሊበን፣ ጎዛምን እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች እንዳለ ተረጋግጧል ነው የተባለው።

የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ይታየው ተስፋሁን በባሶ ሊበን እና ጎዛምን ወረዳዎች ለምንጣፍ የሚሆን 21 ሚሊየን 151 ሺህ 195 ነጥብ 2 ቶን የግራናይት ማዕድን እንዳለ መረጋገጡን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በደብረ ኤልያስ ወረዳ 2 ሚሊየን 438 ሺህ 100 ቶን የግራናይት ማዕድን ክምችት መገኘቱንም ገልጸዋል።

የአማራ ክልል እምቅ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኑን ያስታወቀው ኤጀንሲው፥ ሀብቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.