Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው በሁለት የተለያዩ ቦታዎች የደረሰ ሲሆን፥ አንድ እናት እና የአሽከርካሪ ህይወት ማለፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያን የጠቀሰው የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዛሬ ጠዋት 2 ሰአት አካባቢ ጅጋ ከተማ መንገድ ላይ የነበሩ እናት ከደብረ ማርቆስ ወደ ፍኖተ ሰላም ይጓዝ በነበረ ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ተገጭተው ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በጃቢ ጠህናን ወረዳ ሆዳንሽ በተባለ አካባቢ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከአይሱዙ ጋር ተጋጭቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፥ በሌሎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋው የደረሰበት አካባቢ ከዚህ ቀደም ለሰርግ ይጓዙ በነበሩ መንገደኞች ላይ አደጋ ደርሶ የ7 ሰወች ህይወት ያለፈበት ቦታ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን አሽከርካሪወች የተሽከርካሪያቸውን ደህንነት በመጠበቅ፥ ምንጊዜም ፍጥነታቸውን በመቀነስ እንዲያሽከረክሩና ለእግረኛ ቅድሚያ እንዲሰጡም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.