Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር የተመራ ልዑክ የገበታ ለሀገር አንዱ አካል የሆነውን የጎርጎራ ፕሮጀክት መተግበሪያ አካባቢን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን የገበታ ለሀገር አንዱ አካል የሆነውን የጎርጎራ ፕሮጀክት መተግበሪያ አካባቢን ጎብኝቷል።

በክልሉ ርእሰ መስተዳድር የተመራው ልዑክ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ ባለሀብቶችንና ምሁራንን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በጣና ሐይቅ ዳርቻ በሚገኘው የጎርጎራ ፕሮጀክት የቱሪስት ፍሰትን ለመሳብና የአካባቢ ጸጋን በመጠቀም የተለያዩ ልማቶችን ለመተግበር ታቅዷል።

ዘመናዊ ካፌና ሬስቶራንት፣ የብስክሌትና ፈረስ መጋለቢያ፣ ባህላዊ መንደሮች ልማት፣ የግብርና ምርምር፣ የዓሳ ማስገሪያ መዳረሻን ማልማትና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረግበታል ሲል አብመድ ዘግቧል።

በሀገር ደረጃ 3 መዳረሻዎችን በ3 ቢሊየን ብር ለማልማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮች እየተከናወኑ ነው።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.