Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የአብሮነትና የሰላም ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታ ችግር ተከስቶባቸው በነበሩት የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር የአብሮነትና የሰላም ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።

የአብሮነትና የሰላም ሥነ-ስርዓቱ በከሚሴ ከተማ ደዋ ጨፋ ወረዳ ተረፍ ቀበሌ አስተዳደር እየተካሄደ ሲሆን፥ ሰላምንና አብሮነትን ያስተሳስራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከጥቂት ጊዜያት በፊት የጸጥታ መደፍረስና ከፍተኛ ችግሮች ደርሰውበት የነበረውን የሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንን ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ በተጠናከረ ሁኔታ ለመመለስና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ በአካባቢው የተቋቋመው የጸጥታ ግብረሃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች የሁለቱ ዞኖችና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በሐይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች መሪነት እየተከናወነ የሚገኘው ሥነ-ስርዓቱ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ ለማድረግና ወንጀለኞችን ለማጋለጥ ያለመ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.