Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በሎጐና አርዲቦ ሀይቅ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመታደግ ያለመ የጥናትና ምርምር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በሚገኙት ሎጐና አርዲቦ ሀይቅ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመታደግ ትኩረት ያደረገ የጥናትና ምርምር መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩን የክልሉ መንግስት የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ ኤጀንሲ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ማዘጋጀታቸው ተመላክቷል።
በዚህ መድረክ ላይ ሁለት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች ቀርበው ባለድርሻዎች ውይይት እያደረጉባቸው ነው፡፡
ጥናታዊ ጽሁፎቹ ትኩረት ያደረጉባቸው በሁለቱ ሀይቆች ላይ የተከሰቱትን የአሳ ሀብት መመናመን፣ ብዝሃ ህይወት ጥበቃና መጤ አረምን መከላከል እንዲሁም በሀይቆቹ ዙሪያ በሚከናወኑ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተግባራት ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የአማራ ክልል የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አያሌው ወንዴ÷ በሀይቆቹ ዙሪያ እየተስፋፉ ያሉ የእርሻ ቦታዎች፣ ህገ-ወጥ ግንባታ፣ ከሎጅ አካባቢ የሚወገዱ ቆሻሻዎችና ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ህብረተሰቡ በሀይቆቹ ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኝና ሀይቆቹን ለብክለትና ለውሃ መጠን መቀነስ እየዳረጉ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቱ ፕሬዝዳንት ዶክተር አፀደ ተፈራ በበኩላቸው÷ ይህንን ችግር ተፈፃሚ በሚሆን ጥናትና ምርምር ማገዝ አስፈላጊ በመሆኑ በጥናቶቹ የተገኙ ውጤቶችን ተግባራዊ በማድረግ ችግሮቹን ለመፍታት ከኤጀንሲውና ከአጋሮች ጋር በጥምረት ይሰራል ብለዋል።
በሀይቆቹ ዙሪያ ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለማስቆምና ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ለመስራትና የሀይቆቹን የቱሪስት መዳረሻነት፣ የኢኮኖሚ አመንጭነትና ለአካባቢ ስነ-ምህዳር መጠበቅ በትኩረት እንደሚሰራም የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ ተናግረዋል፡፡
በአንድነት ናሁሰናይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
6
Engagements
Boost Post
6
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.