Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳን በመስኖ ለመሸፈን እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል በ2013 ዓ.ም በመስኖ ልማት ከ247 ሺህ በላይ ሄክታር ለማልማት እየሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ህዳር የመጀመሪያው ሳምንት ድረስ በተለይ በምሥራቅ አማራ 20 ሺህ ሄክታር በሽንኩርት፣ ቲማቲም እና በሌሎች አትክልት እና ፍራፍሬዎች ማልማት እንደጀመረ የቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውኃ አጠቃቀም ዳይሬክተር ይበልጣል ወንድምነው ገልጸዋል፡፡
በ2012 ዓ.ም 218 ሺህ ሄክታር በማልማት 30 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል።
ዳይሬክተሩ በ2013 ዓ.ም 29 ሺህ ሄክታር አዲስ ተጨማሪ ሊለማ የሚችል መሬት በማካተት 247 ሺህ ሄክታር ለማልማት እንደታቀደና 37 ሚሊየን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ ለማምረት ሥራ መጀመሩንም ነው ያስረዱት፡፡
በምስራቅ አማራ 20 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ መልማት መጀመሩ በበረሃ አንበጣው የወደመውን ሰብል ለማካካስ እንደሚረዳም አቶ ይበልጣል ተናግረዋል፡፡
የበረሃ አንበጣ ያደረሰውን ውድመት ለማካካስ የዘንድሮ የመስኖ ስራ በተለየ መልኩ እንደታቀደ ዳይሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል ፡፡
እቅዱን ለማሳካት በየደረጃው ላሉ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን የጠቆሙት አቶ ይበልጣል ÷20 ሺህ 239 ኩንታል ምርጥ ዘር እና 170 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በግብዓትነት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ መግለጻቸውን አብመድ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.