Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአምስት ወራት ውስጥ 8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአምስት ወራት ውስጥ 8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ እንደቻለ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን ገለፁ፡፡

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 20 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ይገኛል።

አፈፃፀሙ በዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው ውስጥ 40 በመቶ ሲሆን በአምስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው ደግሞ 95 ነጥብ 3 በመቶ ነው ብለዋል፡፡

ይህ አፈፃፀም በ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ላይ ከተሰብሰብ ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ጭማሪ ወይም 44 ነጥብ 3 በመቶ ብላጫ አሳይቷል፡፡

የአምስት ወራት እቅዱ መቶ በመቶ እንዳይሳካ የኮቪድ ወረርሽኝ በፈጠረው ተፅኖ እስካሁን ድረስ ያላገገሙ ዘርፎች እንደ ቱሪዝም እና የአገልግሎት ዘርፉም ክፉኛ መጎዳቱ እንደሆነ ሃላፊዋ መናገራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከጸጥታው ጋር ተያይዞ እስካሁንም ድረስ ወደ ስድስት ዞኖች በተገቢው ሁኔታ የተደራጀ ስራ እንዳልሰሩ ነው የተነገረው ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.