Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከሚገኙ 234 ማደያዎች ውስጥ 46 የሚሆኑት ስራ ማቆማቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከሚገኙ 234 ማደያዎች ውስጥ 46 የሚሆኑት አገልግሎት ማቆማቸውን የክልሉ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ከነዳጅ አቅርቦት ስርጭት ጋር በተያያዘ እያጋጠሙ ባሉ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ከሰሜን ሸዋ፣ ከአፋር፣ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን ለመጡ አመራሮችና አጋር አካላት ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ እንደገለፁት÷ በክልሉ ካሉ 234 ማደያዎች 46ቱ አገልግሎት አቁመዋል፡፡

በካፒታል እጥረት፣ በጦርነቱ ምክንያትና በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ፍላጎት አለመኖር፣ በግብይት ወቅት በካሽ መክፈል መጀመሩ ማደያዎቹ እንዲያቆሙ ምክንያት መሆኑን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ከባለሃብቶች ጋር ውይይት በማድረግ ችግሮች ከተለዩ በኋላ ወደ ስራ ያልገቡትን ፍቃድ እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ማደያዎች አናሳ በመሆናቸው ለማስፋፋት እንዲቻል ከ700 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ፍቃድ ተሰጥቷቸው ግንባታ የጀመሩ መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

ፍቃድ ተሰጥቷቸው ምንም ስራ ያልጀመሩትን ደግሞ በማጣራት ወደ ተግባሩ እንዲገቡ እንደሚደረግ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

በሰብለ አክሊሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.