Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዷል

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተያዘው በጀት አመት ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሀይለማርያም ከፍያለው እንደገለጹት÷ በክልሉ 229 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊለማ የሚችል ነው ፡፡

ከዚህም መካከል 100 ሺህ ሄክታሩን በዚህ አመት ለማልማት ታቅዷል፡፡
እንደ ዶክተር ሀይለማርያም ገለጻ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በክልሉ ባደረገው ወረራ 5 ዞኖች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በ2ሚሊየን ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ባደረሠው ጥፋትም 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት ወድሟል ነው ያሉት፡፡

ይህንን ጉዳት ለማካካስም የመኸር ሰብልን ያለብክነት መሰብሰብና መስኖን ከሶስት እስከ አራት እጥፍ ማሳደግ እንደ ትኩረት ተይዟል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም 67 ሺህ ሄክታር ማሣ ለመስኖ የታረሰ ሲሆን ÷37 ሺህ ሄክታር ማሳ ደግሞ በዘር ተሸፍኗል፡፡

ከታረሰው መሬት ውስጥ 27 ሺህ ሄክታር ማሳ ለመስኖ ስንዴ የተዘጋጀ ሲሆን ÷ 1ሺህ ሄክታር በስንዴ ዘር ተሸፍኗል፡፡

በክልል ደረጃ የመስኖ እርሻ ስራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብርም በአዊ ዞን በፋግታ ላኩማ ወረዳ የክልል ግብርና አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የምርምር ማእከላት ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲ ምሁራኖች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በአለባቸው አባተ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.