Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል እየተመዘገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወጣቶች ሰራዊቱን ለመቀላቀል እየተመዘገቡ ነው፡፡
 
በዚህ መሰረትም ከምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ወደ መከላከያ ሰራዊት ለመቀላቀል የተመዘገቡ ወጣቶች ደብረማርቆስ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
 
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውጭ ጠላቶችም ሆኑ የውስጥ ባንዳዎች እየተረባረቡ ባሉበት በዚህ ወቅት የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆን ትልቅ ኩራት መሆኑን ወጣቶቹ ተናግረዋል፡፡
 
የአማራ ወጣቶች ወደ ተቋሙ እንዳይቀላቀሉ የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች ከእውነት የራቁና አማራን ከመጥላት የመነጩ ናቸው የሚሉት ወጣቶቹ÷አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩንን ሉዓላዊት ሃገር በማስቀጠል ታሪካዊ አሻራችንን ለማስቀመጥ ዝግጁ ነን ብለዋል ።
 
አዲሱ ትውልድ ሃገርን የማስቀጠል ታላቅ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣን ትንኮሳም ሆነ ወረራ በመመከት የኢትዮጵያን ትንሳኤ እውን እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡
 
በዚህ ታሪካዊ የሃገር ጥሪ የክልሉ ወጣቶች እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.