Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት አድርጎ እየሰራ ነው-መርማሪ ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ) በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ገለጸ፡፡
 
ቦርዱ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈዋል ተብለው ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በባሕርዳር፣ ጎንደር እና ደብረታቦር ከተሞች ምልከታ አድርጓል፡፡
 
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ የክልሉ የፀጥታ እና ጥበቃ ኃይል አዋጁን ተላልፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ዜጎችን ሲይዝም ሆነ ጥበቃ ሲያደርግ አዋጁን መሰረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
 
የፀጥታ አካላት ተጠርጣሪዎችን ሲይዙ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጡ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ መሆኑን ሰብሳቢው ከተጠርጣሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ማረጋገጥ መቻላቸውን ነው የገለጹት ፡፡
 
ለነፍሰ-ጡሮች ፣ ለሚያጠቡ እናቶች ፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ቅድሚያ ምርምራ እንደሚደረግላቸው እና ንጹሃን እየተለቀቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
 
በተጨማሪም ስምንት ሰዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው የተሟላ የመኝታ አገልግሎት ማግኘታቸውን፣ የውሃ እና መጸዳጃ አገልግሎት መኖሩን፣ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች እንግልት እየደረሰባቸው አለመሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
በሌላ በኩል ማሕበረሰቡ ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎችን ንብረት ከዘራፊዎች እየጠበቀ መሆኑን፣ የፀጥታ ሃይሉ ሕጋዊ አሠራሮችን በተከተለ መንገድ ተጠርጣሪዎችን እያስተናገደ መሆኑን እና በማጣራት ሂደት ንጹሃን እየተለቀቁ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
 
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው፥ መርማሪ ቦርዱ ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ በጉብኝት ሂደቱ ያስተዋላቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰራ መግለጻቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.