Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 20 ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል 20 ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱን የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው÷ በሽታው በስፋት ይከሰትበታል ተብለው ከሚጠበቁ ወራቶች ቀድሞ መስፋፋት ጀምሯል።
በኢንስቲትዩቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ አብርሀም አምሳሉ÷ አሁን ላይ በክልሉ 20 ወረዳዎች ላይ በበሽታው ሰዎች እየታመሙ ነው ብለዋል።
በሽታው የታየባቸው በስፋት በምእራብ አማራ ያሉ እንደ ምእራብ ጎንደር ፣ማእከላዊ ጎንደር፣ደቡብ ጎንደር፣ምእራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች መሆናቸውን አንስተዋል።
ቦታዎቹም ለበሽታው አጋላጭ የሆኑ ሰፋፊ የልማት ቦታዎች ፣ውሀማ ቦታዎች በስፋት የሚገኙባቸው፣ከልማት ኮሪደር ጋር ተያይዞ የሰዎች እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው መሆን አሁን ላይ ለበሽታው መስፋፋት እንደ ምክንያት ከቀረቡት ተጠቃሾቹ ናቸው።
በሽታው ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው መተማ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
በክልሉ ያለውን የወባ በሽታ ለመቀነስ የቀረቡ ግብአቶችን የማሰራጨት ስራዎችም እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በ 59 ወረዳዎችም 2 ነጥብ 7 ሚሊየን አጎበር እየተሰራጨ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ÷ የኬሚካል ርጭት ስራም መስራት መጀመሩን ገልጸዋል።
45 ያህል ወረዳዎችም ቀድሞ የኬሚካል ርጭት እንደተከወነባቸው ነው አቶ አብርሀም የነገሩን።
ክልሉ በሽታው በስፋት የሚገኝባቸው አካባቢዎች ላይ የጤና በለሙያዎች የቤት ለቤት የምርመራና የህክምና ስራዎችን ለማከናዎን ወደ ስራ ተገብቷልም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።
በሽታውን ለመቀነስ በተቋም ደረጃ ከሚሰሩ የመከላከል ስራዎች በተጨማሪ የተሰራጩ አጎበሮችን በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም ለወባ ትንኝ መራቢያ የሚሆኑ ቦታዎችን ማስወገድ እና መሰል ጥንቃቄዎችን በማድረግ ህብረተሰቡ የበኩሉን ግድታ እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
የወባ በሽታ ህክምና በመንግስት ተቋማት በነፃ እየተሰጠ መሆኑን ያሳወቀው ኢንስቲትዩቱ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሁሉ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ እንዲታከምም አሳስቧል።
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.