Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 500 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል ህወሓት እየፈጸመ ያለውን የአሸባሪነት ወንጀል የሚያጋልጥ የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተጀመረ።

በፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄው 500 ሺህ ሰዎች ተሳታፊ ሲሆኑ÷ ንቅናቄው “ነጩ ፖስታ፤ ለነጩ ቤተ መንግስት” በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የፊርማ ማሰባሰብ ስነ ስርአት ለመቀላቀል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ በፊርማ ማሰባስቢያ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ እንዳሉት÷ የህወሓት አሸባሪ ሃይል የአማራና የአፋር ክልሎችን በመውረር መጠነ ሰፊ ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ፈጥሯል።

ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ፣ ዜጎች ለዘመናት ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በማውደም፣ ከህጻናት እስከ አዛውንት ያሉ ሴቶችን መድፈር ጨምሮ ሌሎች ግፎችን መፈጸሙን ተናግረዋል።

“ወራሪው ሀይል በአማራ ክልል በማይካድራ፣ አጋምሳና ጭና እንዲሁም በአፋር ክልል ጋሊኮማ ላይ ንፁሃ ን ዜጎችን በመጨፍጨፍ አሸባሪነቱን በተግባር አረጋግጧል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.