Fana: At a Speed of Life!

በአማዞን ደን ላይ የሚካሄደው ምንጣሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብራዚል በአማዞን ደን ላይ እየተካሄደ ያለው የደን ምንጣሮ ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

በሃገሪቱ እየጨመረ የመጣው የእርሻ መስፋፋትና የእንስሳት ግጦሽ ለደን ምንጣሮው ዋነኛ ምክንያት መሆኑም ይነገራል፡፡

ይህን ተከትሎም እድሜ ጠገብ ረጃጅም ዛፎች እየተቆረጡ የደኑ ስነ ምህዳርም ክፉኛ እየተጎዳ ነው ተብሏል፡፡

ከነሐሴ 2019 እስከ ሐምሌ 2020 ድረስ ብቻ 11 ሺህ 88 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ወይም 4 ሺህ 281 ስኩዌር ማይል ደን ወድሟል ነው የተባለው፡፡

ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ9 ነጥብ 5 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

አንዳንድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ግን በደኑ ላይ እየደረሰ ያለው ጥፋት እየቀነሰ ነው በሚል መረጃውን ለማስተባበል ሞክረዋል፡፡

በርካቶች ግን ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በአማዞን ላይ የከፋ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በደኑ ውስጥ እርሻና የማዕድን ቁፋሮ ይካሄድ ዘንድ ይሁንታ መስጠታቸውና ደጋፊ መሆናቸው ይነገራል፡፡ እርሳቸው ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ ባለው የፈረንጆቹ 2018 ላይ 7 ሺህ 536 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የደኑ ክፍል መመንጠሩን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

አማዞን ደን ለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ጥብቅ ደን ነው፡፡

አማዞን ደን ወደ 3 ሚሊየን ለሚጠጉ የእጽዋት እና የእንስሳት ዝርያዎች መኖሪያ ስፍራ ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.