Fana: At a Speed of Life!

በየመን በአደጋ ከሞቱት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ማንነት ለማወቅ እየተሰራ ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን እስር ቤት ውስጥ በተነሳ አመፅና የእሳት አደጋ ከሞቱት ሰዎች መካከል ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ማንነት ለማወቅ እየተሰራ ነው መሆኑን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንቱ በሃገር ውስጥና በውጭ የተከናወኑ ጉዳዮችን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሳምንቱ ከፓለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ ኢትዮጵያ የተሻለ ግንዛቤ የፈጠረችበትን አቋም ያንፀባረቁ ውይይቶችን ማከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትና ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ግንኙነት ላይ ያደረጉት ውይይት ስኬታማ እንደነበር ገልፀዋል።

በሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያረገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጣልቃ ገብነቶችን በመቃወም  ያደረጓቸው ሰልፎች በሃገር ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚል ዜጋ እየተፈጠረ መምጣቱን ያመላከተ ነበር ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ለተጎዱ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች እስካሁን የመጀመሪያ ዙር የምግብና እርዳታ ተደራሽ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በሳምንቱ ከ40 ሃገራት የተውጣጡ አምባሳደሮች ወደ ትግራይ እንዲጓዙ መደረጉንና አምባሳደሮቹም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ማውጣታቸውን በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ በየመን እስር ቤት ውስጥ በተፈጠረ አመፅና የእሳት አደጋ 43 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የኢትዮጵያውያን ማንነትን ለማጣራት መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ አደጋው በደረሰበት የመንም የተቀሩት ዜጎቿን የማውጣት ስራ እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ዛሬም እኩለ ቀን አካባቢ 150 ኢትዮጵያውያን ከኤደን ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ እንደሚጓዙ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሳምንቱ 888 ዜጎቿን ከሳውዲ ዓረቢያ-ጅዳ ወደ ሃገር ቤት መመለሷን ያነሱት ቃል አቀባዩ፤ የኢትዮጵያውያን ሟቾች ትክክለኛ ቁጥርና ማንነት እስካሁን በግልፅ ባይታወቅም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘንም ገልጿል፡፡

በሶዶ ለማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.