Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውንና የተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ አሪዞና እና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ፡፡
በአሜሪካ አሪዞና ግዛት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለተፈናቀሉት ዜጎች 110 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መሰበስቡን ኢዜአ ከድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ የኢትዮ-ካናዳውያውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ) የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ቻፕተር አሸባሪው ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከ80 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ መሰብሰቡን ሰብስቧል፡፡
በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ተፈናቅለው በባህርዳር ለተጠለሉ ተፈናቃዮች 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ 500 ሜትር ብትን ጨርቅ፣ ከ100 በላይ ጥንድ ጫማዎች፣ 400 ካርቶን የምግብና ከአንድ ሺህ በላይ የልብስ ማጠቢያዎችን ያካተተ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ ተፈናቃይ ወገኖችና የጸጥታ ኃይሎችን በራስ አቅም መደገፍ የዲፕሎማሲ ጫናውን ለማቃለል ይረዳል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ መስፍን በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ደርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀና አርዓያ ሥላሴ ዜጎችን ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት እገዛቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራውን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ደርጅት ስራተኞችና አመራሮች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.