Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሩብ ሚሊየን አልፏል፡፡

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 250 ሺህ 29 የደረሰ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 11 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚጠጋ ነው የጆን ሆፕኪንስ መረጃ የሚያመላክተው፡፡

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ከተጎዱ ሃገራት መካከል ዓለም ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ56 ሚሊየን 564 ሺህ በላይ ሲሆን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ1 ሚሊየን 354 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ሩሲያ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚዎች ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.